የሰው ልጅ #ሥጋና #ነፍስ ነው፡፡ ሥጋ ብቻውን በድን ነው፡፡ ሬሳም ይባላል፡፡ ነፍስ ብቻዋን በዚህ ምድር ላይ አትገለጥም፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እንዲያ አይደለም፡፡ ለነፍስ ሥጋ ያስፈልጋታል፣ ለሥጋ ነፍስ ታሻዋለች፡፡ ያዕ.2፣26
“ሰው” የምንለው – “ሰብእ”ን ነው፡፡ “ሰብእ” ግዕዝ ነው፡፡ “ሰብአ” ይወጣዋል፡፡ “ሰባት” ነው፡፡ ሰባት ምኖች ቢሉ፣ ባሕርያት፡፡ ማን ናቸው ቢሉ መሬታዊነት፣ ነፋሳዊነት፣ እሳታዊነት፣ ውኃዊነት፣ ለባዊነት፣ ነባቢነት እና ሕያውነት ናቸው፡፡
ሰባቱ ሁለት ቦታ መኾን ይችላሉ፡፡ ዐራቱ ባንድ፣ ሦስቱ በሌላ፡፡ የቀደሙት ዐራቱ ሥጋዊነታችን ይጠቀልላቸዋል፡፡ የሚከተሉት ሦስቱ ግን የነፍሳችን ናቸው፡፡
ሰው በሥጋው እንስሳትን በነፍሱ መላእክትን ይመስላል፡፡
እንስሳት እንደሰው ቢመስሉ ቅሉ ሕያዊነት፣ ነባቢነትና ለባዊነት ይጐድላቸዋል፡፡ በጥቅሉ ሕያዋን ዘላለማውያን አይደሉም፡፡ መንግሥትም፣ ጽድቅም፣ ልጅነትም፣ ጸጋም ለእነርሱ የሏቸውም፡፡ ደመ ነፍስ እንጂ ነፍስ የለቻቸውም፡፡
መላእክት እንደሰው ቢመስሉ ቅሉ ሥጋዊ ባሕርይ ይጐድላቸዋል፡፡ አይበሉም፣ አይጠጡም፣ አይደክሙም፣ አይተኙም … መናፍስት ናቸውና፡፡ መንፈሰ ሕይወት እንጂ ሥጋ ለእነርሱ የላቸውም፡፡
ሰው ግን አንድም እንስሳዊ አንድም መልአካዊ ባሕርያትን ገንዘብ አድርጓል - ማለት እኒያ ሁለቱ የኾኑትን እርሱም ደግሞ ኹኗል፡፡ እንደ እንስሳት ይበላል፣ ይጠጣል፣ ይደክማል፣ ይተኛል፣ በሩካቤ ደግሞ ትፍስሕትን - ማለት - የሥጋ ደስታ ያገኛል፡፡ እንደ መላእክት ደግሞ ያመልካል፣ ያመሰግናል፣ ልብ ያደርጋል፣ ይናገራል፣ ሕያው ኹኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡
ከሁለቱም በላይ ደግሞ ልጅ ተብሏልና ወደፊት መንግሥቱን ይወርሳል፡፡
እንስሳዊ ባሕርያታችን ሥጋችን ላይ የተለጠፉ፣ የዚህ ዓለም ብቻ እንጂ ሞታችንን ተሻግረው የሚሄዱ አይደሉም፡፡ መልአካዊ ባሕርያታችን ነፍስ ላይ የተለጠፉ፣ ሞትን መሻገር የሚችሉና ወዲያ የሚከተሉን ናቸው፡፡
በጾም ወቅት እንስሳዊውን ባሕርያችንን እየጐሰምን መልአካዊ ባሕርያችንን እናገንናለን፡፡ ምድራዊነታችንን እየለጐምን ሰማያዊነታችንን እናመክራለን፡፡ ሞት የሚይዘውን ባሕርይ እየደቈስን ሞት የማይገታውን ባሕርይ እናመክራለን፡፡ መቃብር የማይሻገረውን ደስታችንን ገትተን መቃብር የማይመልሰውን ደስታችንን እኰተኩታለን፡፡ ከመብላት የዋሐትን፣ ከመጠጣት ርኅራኄን፣ ከመተኛት ምስጋናን፣ ... ከትፍስሕተ ሥጋ ፍስሐ ነፍስን እንታጠቃለን፡፡
ነፍስ መልአካዊነቷ የሚበረታ ደግሞ ሥጋ እንስሳዊነቱ ሲጐሰምበት ነው፡፡
የሥጋ ተድላ ሲያይል ነፍስ ትሸፈናለች፡፡ ሥጋዊነት ሲበረታ መንፈሳዊነት ይዝላል፡፡ ነፍስ ስትደክም እግዚአብሔር ይትተዋል፡፡ የሥጋ ምቾት ቅጥ ማጣት እግዚአብሔርን ያስንቃል፡፡
--- “የእርሻውን ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤ የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውም ወተት፥ ከጠቦት ስብ ጋር፥ የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።” -- ዘዳ.32፣13-15
ጾም ግን የነፍስን ቊስል ትፈውሳለች
ሥጋ ሲደክም ነፍስ ትበረታለች፣ ሥጋ ሲጠወልግ ነፍስ ትገንናለች፣ ሥጋ ሲጐሰም ነፍስ ታይላለች፣ ሥጋ ሲቀጣ ነፍስ ትጐላለች፣ ሥጋ ሲከስም ነፍስ ትታያለች፡፡ ከምንመገብ ይልቅ ስናመሰግን፣ ከምንጠጣ ይልቅ ስንቀድስ፣ በፍትወት ከምንረካ ይልቅ በምስጋና ሐሴት ስናደርግ ይልቁኑ ሰማያውያን እንመስላለን፡፡ ከነፍሱ ይልቅ ሥጋውን የሚወድድ ከሰማያዊ መንግሥት ይልቅ ምድራዊ ተድላን ይመርጣል፡፡
በዚህ ምክንያት እንጾማለን፡፡
የቃልን ሥጋ መኾን እያሰባችሁ ጹሙ! የእግዚአብሔርን መጎብኘት! የወልድን ትሕትና! የአዳምን ልዕልና እያሰባችሁ ጹሙ፡፡ የአምላክን ሰው መኾን፣ የሰውን አምላክ መኾን እያሰባችሁ ጹሙ! የመጐብኘታችንን ዘመን! ሐዲሱን ኪዳን እያሰባችሁ ጹሙ! መልካም ሰሙነ ሱባዔ ለኹላችሁ፡፡

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ