ቀዳማዊት እና ዳግሚት ሔዋን

ሁለቱም #ሔዋኖች መላእክት መጥተውባቸው ነበር። ሁለቱም ሔዋኖች የተነገራቸው ዜና ታላቅ እንደሚኾኑ ነበር፤ #የቀደመችዋ አምላክ#ዳግሚቷ እመ አምላክ፤ ሁለቱም አጋጣሚ ጽኑ #እምነት #ከትሕትና ጋር ይጠይቅ ነበር።

የቀደመችቱ ክብሩን ሰምታ ቋመጠች፤ ዳግሚት ግን ይህ እንዴት ይኾንልኛል አለች። የቀደመችቱ ትጠየቅ ነበር እንጅ አትጠይቅም፤ ዳግሚት ግን ኹሉን ትመረምር አበክራም ትጠይቅ ቆፍጣና መልስም ትጠብቅ ነበር። ያሃቺ የተባለውን ለመኾን ተጣደፈች፤ ይህች ግን እኔ ባርያ ነኝ ብላ ራሷን አዋረደች። ያች እምነቷ ጎዶሎ ነበር፤ ይህች የጌታዋን ቃል ያመነች ብጽዕት ነበረች። ያች ትዕቢተኛ ነበረች፤ ይህች ትሑት። ስለዚህም ያችን ጌታ አምላክነትን ስለፈለገች ባርነትን ሰጣት ባልሽ ይግዛሽ አላት። ይህችን ጌታ ባርነትን ስለመረጠች እናቱ አደረጋት እናትነትን ከድንግልና ጋር አንድ ላይ አስማማላት።

ያሃች የሞትንና የኃጢአትን በር ገርበብ አድርጋ ውድቀትን ወጠነችልን፤ ይህች ቤዛ ወልዳ እንካችሁ አለች - ቀርነ መድኃኒታችን ተያዘባት። ያሃች ወደባሕርያችን የሞትን አበጋዝና የሲዖልን ጭሬሮች ጋበዘቻቸው፤ ይህች የሞታችንን ገዳይ የትንሣኤያችንን በኲር ወለደች። በዚያች አዳም ስቶ ኃጢአት፣ በኃጢአትም ሞት ተጠናወተን። በዚህች #ዳግማዊ_አዳምተሰጥቶ ጸጋን ለበስን።

#በሔዋን አለማመን ትቢያ ወደቅን፤ #ሴቲቱ ግን ዘሯን አስነሥታ በእባቡ ላይ በጠላትነት ዘመተችበት። ኦ #ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዐብየኪ፤ እስመ ወለድኪ ለነ #መብልዓ_ጽድቅ ዘበአማን#ወስቴ_ሕይወት ዘበአማን።

አስተያየቶች