እምነት ማለት ሰው ከእርሱ ውጪ ያለውን “ነባራዊ ኹነት” ወይም “የእውነታውን ዓለም” የሚያስረዳበት የመንሥዔና ውጤት ስልታዊ ቅንብር ነው፡፡ የሚታየውና የማይታየው ኹሉ የኾነበትን ሂደት፣ ትርጕሙን፣ የተቀመጠለትን ዓላማና ፋይዳዎቹን በሚመለከት የሚያስቀምጣቸው የተለያዩ የእውነታ መጠይቆች ስብስብ (Set of truth claims) ነው፡፡
.
የኾነውን ኹሉ የምናስረዳበት ብቸኛው መንገድ ግን እምነት ብቻ አይደለም፡፡ በስሜት ሕዋሳት በመጠቀም በማየት፣ በመስማት፣ በመቅመስ፣ በማሽተት፣ በመዳሰስ በእነዚህ በአምስቱ የምንቀስመው ተለምዷዊ እውቀት (Sensory experience) ሕዋሳቱ ደርሰው ሊያውቁት የሚችሉትን ውሱን የኾነ የሚታየውን ዓለም ማስረዳት የሚችል ሲኾን “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” -- ዕብ.11፥1
.
ስለዚህ ልብ ብለን ካስተዋልን ለምሳሌ ያክል የማያምኑ ሰዎች በሳይንስ የተገኘ እውነት ማለት በሰው አቅም ሊደረስ የሚቻልበትንና በስሜት ሕዋሳት በመጠቀም ሊታወቅ የሚችለውን ዓለም (እውነት) ብቻ “እውነት” ይሉታል ማለት ነው፡፡ ለአብነት ያክል እንኳ የሕዋና የጠፈር ሳይንስ የሚችለውን ከዚሁ ኹኖ አነጣጥሮ ተመልክቶ፣ የማይችለውን ደግሞ
.
ስለዚህ “እውነት” የሚባለውን ነገር ሲተረጒም የሰው ልዥ በሰብአዊ ተፈጥሮው መድረስ በሚችልበት ገደብ ልክ አጥብቦ የደረሰበትን ይተረጕማል ማለት ነው፡፡ ቀሪው “መላ ምት” (hypothesis) ነው ማለት ነው፡፡ ፈረንጆቹ ይህን ኹሉ “Reason” ይሉታል፡፡ “አመክንዮ” ለማለት ይቻላል፤ ይህ አመክንዮአዊ እውቀት/እውነት ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በጐላ በተረዳ የታየ የተደመጠ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ውጤት ከጊዜ ወደጊዜ የሚለወጥ እንደሰው ብስለት የሚቀየር መኾኑን ልብ ይሏል፡፡ በአንድ ወቅት ሳይንሱ ፀሐይ በምሥራቅ ወጥታ ዙራ በምዕራብ ትጠልቃለች፤ ምድር ቀዋሚ ናት ይል ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተቀይሮ ፀሐይ አትወጣም፤ አትገባምም፤ ቀዋሚ ናት፡፡ ይልቁን ምድር ትዞራለች ይላል፡፡ ነገ ምን እንደሚል አይታወቅም፡፡
.
ሳይንሱ ከሃይማኖት ጋር የሚለያየው ታዲያ ለ“እውነት” በሚሰጠው በዚህ ጠበብ ባለ ፍቺው ነው፡፡ ያልተደረሰበት ወደፊት በምርመራ ሊገኝ የሚችል እውነት ሊኖር እንደሚችል እሙን ኹኖ፣ ነገር ግን ማንኛውም “እውነት” ሳይንሱ “እውነት” ብሎ ወደሚጠራው ጥቅል “እውቀት” ለመግባት ይህን ስልተ ምክንያታዊ ሙከራ (logical test) ማለፍ አለበት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሳይንስ ዓይኑ የገባውን፣ ዠሮው ያዳመጠውን “እውነት” ይላል ማለት ነው፡፡ ከዚያ ሌላ እውነት የለውም ነው፡፡
.
ወደ ሃይማኖት ስንመጣ ግን ይህ አመክንዮአዊ እውነት ጥቂቱ እውነት ብቻ ነው፡፡ ሲቀጥልም ዋናውም እውነት አርሱ አይደለም፤ የቀረ ሌላ እውነት አለ፡፡ የሚበልጥ አለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህን አመክንዮአዊውን እውነት ሲመሠርት (የሚታየውንና የማይታየውን ኹሉ ሲፈጥር) የሰውን ልዥ ወደዚያኛው፣ ምልዓት ወዳለው፣ የሚሰፋ እውነት እንዲወስደን በማሰብ እንጂ ርሱን ብቻ መርምሮ፣ ርሱኑ ብቻ አድንቆ በርሱው ተመስጦ፣ ቊም ነገሩ ርሱ መስሎን እዚያው ለመቆም አይደለም፡፡
.
በተለይም ደግሞ “ኢቊስ አካላዊውን ዓለም” (Immaterial worldን - ቊስ አካላዊ ያልኾነውን ዓለም ለማለት ነው) የሚመለከተው እውነት/እውቀት በአመክንዮ መረዳት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የሳይንቲስቶችን የራሳቸውን መሠረተ አሳብ ካየን እንኳ ማንኛውም ነገር አምስቱ ስሜት ሕዋሳት ውስጥ ለመግባትና በእነርሱ ተለይቶ ህላዌው (መኖር አለመኖሩ) እንዲታወቅ ያሃ ነገር ተፈጥሮው “ቊስ አካላዊ” (Material being) መኾን አለበት፡፡
.
ቊስ አካላዊ (Material being) ማለት ከቊስ (ከmatter) የተገነባ የተዋቀረ ማለት ነው፡፡ (something which is composed of matter)፡፡ በዚህ ፍልስምናዊ አፈታት ከኾነ ማንኛውም ቊስ አካላዊ ኹነት ከርሱ ከሚያናንሡ ሌሎች አላባውያን ተዋቅሮ ተገንብቶ የተሠራ ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ደግሞ የቊስ አካላዊው ዓለም ዓይነተኛ መገለጫ ነው፡፡
.
የሰውን ልዥ እንኳ ብንመለከት በሥነ ደቂቅ አካላዊ ጥናት
(particle physics) የተለያዩ እንደ ልብ፣ ኩላሊት፣ ሳንባ፣ ደም፣ አጥንት ወዘተ ያሉ “ብልቶች” (organs)
የፈጠሩት ማኅበር ነው፡፡
ብልቶች (organs) ደግሞ ጡንቻዎች ተያይዘው ተዋሕደው የፈጠሯቸው ናቸው፡፡ ጡንቻዎች (muscle) ደግሞ “ኅብረ ሕዋሳት” (tissues) በተለምዶ “ሥጋ” የምንላቸው ተባብረው አብረው
የፈጠሯቸው ናቸው፡፡ “ኅብረ ሕዋሳትን” (tissues) ደግሞ ሕዋሳት (cells) ብዙው በአንድ ኹነው
የፈጠሯቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ የተለያዩ “መትሕተ ሕዋስ አዋቃሪዎች” (organelles) ያሏቸው ጥቃቅን አካላት ናቸው፤ ሕይወት
የሚዠምረው እዚህ ደረጃ ነው፡፡ “መትሕተ ሕዋስ አዋቃሪዎች” (organelles) ደግሞ ብዙዎች “አቶሞች” ባንድ እየተጠጉ በኬሚካዊ ጥምረት (chemical bond) እየተያያዙ ከፈጠሯቸው “ኅብረ አቶሞች” (molecules) የተሠሩ ናቸው፡፡ አቶሞች የምንላቸው ደግሞ
የተወሰኑ “ማእከላውያን የኃይል ቅንጣቶች” (protons and neutrons) እና በዙሪያ የሚዞሩ “እለ ቄጠሮናዊ ቅንጣቶች” (electron) ጥምረት ውጤት ናቸው።
.
ሰውን ብቻ አየን እንጅ ዓለም በሙሉ ሕይወት ያለውም የለለውም ግዑዙም ግዕዛኑም ኹላቸው (material object) በዚሁ ኹኔታ ተዋቅረዋል። ሰማይ ወጥተን ከዋክብቱን ጥልቅ ወርደን ዐሣቱን ብንመረምር እሊህ ታናናሽ ቅንጣቶች በተለያየ አኋኋን እየተቀናበሩ ያመጧቸው ናቸው፡፡ አምስቱ ሕዋሳት ሊለዩትና ሊረዱት የሚችሉትም ዓለም ይህንኑ ቊስ አካላዊ የኾነ ውቅር ዓለም ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ሌላውን እንዴት እናውቀዋለን? … ???
.
ሌላ ምንም ልናውቀው የሚገባ እውነት/እውቀት የለም የሚሉ አሉ፡፡ እሊህ ደግሞ ፍልስምናቸው በደምብ ነጥሮ ሲቀመጥ ጠቅለል ባለ ልሳን “ከሚታየው፣ ከሚሰማው፣ ከሚሸተተው፣ ከሚቀመሰው፣ ከሚዳሰሰው ኹነት ውጪ ኹነት የለም” የሚሉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የለም ለማለት ነው እንግዲህ፡፡ እሊህ ሰዎች እውነትን ወደዚያ ወዳልነው፣ በስሜት ሕዋሳት ተለይቶ ሊታወቅ ወደሚችለው ነባራዊ ዓለም ብቻ የሚያጠብቡ ናቸው ማለት ነው፡፡ “እግዚአብሔር አለ” ብንላቸው እሊህ ሰዎች መልሳቸው ሊኾን የሚችል “አሳየኝ!” “ድምጡን አስደምጠኝ!” “ልንካው!” ነው፡፡
.
ይህ በእጅግ ቀላል አኋኋን ስሕተቱ ሊገለጥበት ይቻላል፡፡ ኹነቶች ኹሉ አሉ የሚባሉት የግዴታ የሚታዩ፣ የሚሰሙ፣ በስሜት ሕዋስ የሚለዩ ሲኾን ብቻ ከኾነ፣ እሊህ ሰዎች ራሳቸው መኖራቸውን የማይከዷቸው ነገሮች ነገር ግን በሕዋሳት የማይገቡ፣ የማይለዩ “ኢቊስ አካላዊ” ኹነቶች (immaterial beings) አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል “እውነት/እውነታ” (Truth/Reality)፣ “እውቀት” (Knowledge)፣ “ፍቅር” (Love/Compassion)፣ “ጥበብ” (Wisdom) ወዘተ. እሊህ ነገሮች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የሚታዩ የሚዳሰሱ ነገሮች አይደሉም፡፡ በዚህ ምክንያት የእኒህን ነገሮች መኖር ሲያስረዱ ሰዎች በቀጥታ አእምሮ-እም-ልማዳዊ (sensory experience) ሳይኾን የሚጠቀሙት ከዚህ ውጭ የኾነ ሌላ መለኪያ ነው፡፡ ለዚህ ነው “እግዚአብሔር” ለሚባለውም ኢቊስ አካላዊ ኹነት (immaterial being) ከስሜት ሕዋሳት ሌላ ማስረጃ ሊጠየቅለት የሚገባ፡፡
.
“እምነት” ደግሞ ተስፋ ስለሚደረጉ እንጂ ለማየት ስለማይቻሉ ነገሮች የሕዋሳትን ቦታ ተክቶ አስረጂ የሚኾን ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል እግዚአብሔር አለ ብሎ ማመን “እምነት” ነው፡፡ ይህን የእውነታ መጠይቅ (truth claim) በስሜት ሕዋሳት፣ ወይም “በአእምሮ-እም-ልማዳዊ” ሂደት (sensory experience) (በተለምዶ ከሚታወቅ ነገር በመነሣት) ለማስረዳት አይቻልም፡፡
.
“ውሻ” እንዳለና እንደሌለ ማንም ሰው ከልምዱ ተነሥቶ መናገር ይችላል፡፡ አይቶ የሚያውቅ ከኾነ አለ ነው፡፡ ሌሎቹንም የቊስ አካላዊው ዓለም አላባዎች (elements of the material world) ህልውናቸውን (መኖር አለመኖራቸውን) በዚህ አኋኋን ማስረዳት ይቻላል፡፡
.
የእግዚአብሔርን መኖርና አለመኖር ስናስረዳ ግን ከቊስ አካላዊ የአተያይ አንጻር (material worldview) ፍጹም መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚባለው ነገር በዚህ ሰማይ ላይ በእውነት ካለ ሳይንቲስቶቹ ራሳቸው እንደሚሉት ከኾነ እርሱ ቊስ አካላዊ (Material Being) አይኾንም፡፡ እግዚአብሔር ቊስ አካላዊ (Material being) ከኾነማ እግዚአብሔርነቱ እዛው ጋር ይቆማል፡፡ ምክንያቱም በባሕርዩ ምሉዕ፣ ስፉሕ፣ ፍጹም ስለኾነ ከርሱ ከሚያንስ ጥቃቅን ነገሮች የተሠራ፣ የተዋቀረ ሊኾን አይችልም፡፡ (ፈረንጆቹ እንደሚሉት Composed nature የለውም፡፡) ከኹሉም በላይ ደግሞ በእንዲህ ያለ ባሕርይ ኹኖ ቊስ አካላዊውን ዓለም እም-ኀበ-አልቦ-ኀበ-ቦ (ካለመኖር ወደመኖር) አምጥቷል ማለት አይቻልም፡፡ ቊስ አካላዊ ኹነት ኢቊስ አካላዊ ኹነትንም ኾነ ሌላ ቊስ አካላዊ ኹነትን ማምጣት አይችልም፡፡
.
በዚህ ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ኢቊስ አካላዊ አካል ከስሜት ሕዋሳት የመረዳት ወሰን ውጪ መኾን ስላለበት የእርሱን ህልውና ለማስረዳት በስሜት ሕዋሳት በኩል ከሚኾን አመክንዮአዊ ሚዛን ውጪ ሌላ ሚዛን እንፈልግለታለን ነው፡፡ ያሃ ሚዛን ቤተ ክርስቲያን “እምነት” ትለዋለች፤ ስለዚህ ይህን ተስፋ የምናደርገውን ነገር እናምነዋለን ማለት ነው፡፡

እዚህ ጋር አንድ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ነገር እግዚአብሔር አለመኖሩን መናገር
በራሱ ስልተ ምክንያታዊ ውድቅነት (ሎጂካል ፌይሉር) ያለበት አስተሳሰብ ነው፤ ወይም ክርክሩ ራሱ ራሱን ደፍቶ ይጥላል፡፡ ምክንያቱም
እግዚአብሔር የለም ለማለት አንድ ሰው የለም የተባለው አካል ባሕርዩ ረቂቅ፣ በኹሉም ቦታ ያለ፣ ስፉሕ፣ ፍጹም ከመኾኑ አንጻር የት
የት ቦታ ፈልጎ አጥቶት ነው ያስብላል፡፡ ምሉዕ በኵለሄ የኾነን ባሕርይ የለም ብሎ ለመናገር እዚህች አፍሪቃ ላይ ቊጭ ተብሎ አይቻልም፤
ውቅያኖስን በርብሮ፣ የተራሮችን ራስ መዝብሮ፣ ጫካውን በትኖ፣ መሬትን ቈፍሮ ኹሉም ቦታ አይቶ “እግዚአብሔር የለም” ማለት አንድ
ነገር ነበር፡፡ ከዚያም ግን ከፍ ብሎ ሰማያትን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን፣ ዓለማትን ኹሉ ሂዶ ፈትሾ ዝቅ ብሎ የበርባሮስን ጥልቅ ቃኝቶ
ከዚያ በኋላ “የለም” ማለት ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡
.
ይህን ያለማመን ትምህርት በልበ ምሉዕነት ለመናገር (ማለትም እግዚአብሔር ሊኖርባቸው
ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ቦታዎችን ኹሉ ፈትሾ ማረጋገጥ) ሰብአዊ ባሕርያችን አያስችለውም፤ ውሱን ፍጥረታት ስለኾንን፡፡ ስለዚህ
“እግዚአብሔር የለም” ባዩ ሰው በሌላ ቋንቋ ይህን ኹሉ የቤት ሥራ አጠናቅቄአለሁ ማለቱ ነው ነው፡፡ ይህን ማድረግ ከቻለ ደግሞ
እርሱ ራሱ ሰው ሳይኾን በኹሉም ቦታ መገኘት የሚችል፣ ኹሉንም ማወቅ የሚችል፣ ከሃሌ ኵሉ “እግዚአብሔር” የሚባልን ስፉሕ፣ ምሉዕ፣
ፍጹም አካል መመርመር የሚያስችል ዘኢየኃልቅ (የማያልቅ)፣ ዘኢይትገመር (የማይቻል/የማይያዝ) ገደብ የለሽ ኃይል ያለው አንዳች
“ልዕለ-ተፈጥሯዊ” አካል ነኝ ማለቱ ነው፡፡ እንደዚህ ከኾነ ደግሞ እርሱ ራሱ “እግዚአብሔር” ነው ማለት ነው፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር”
አለ፡፡
.
በዚህ ምክንያት “እግዚአብሔር የለም” የሚለው ክርክር ራሱ ፈረንጆቹ “ሰልፍ ዲፊቲንግ”
ወይም ራሱን በራሱ ድል ነስቶ የሚጥል ጽንሰ አሳብ ይሉታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የሚሉትን ሰዎች “አብድ” ትላቸዋለች፤ ሰነፍ
ማለት ነው፡፡ ቢያንስ ክርክራቸው ራሱ እስከ ጥጉ ድረስ ተሂዶ ሲመረመር በራሱ ራሱን አንቆ የሚጥል መኾኑ አልታያቸውምና፡፡
.
ሳይንሱ በዚህ አኋኋን አመክንዮአዊ እውነትን (Truth based on Reason) ብቻ እቀበላለሁ ይበል እንጂ ምንም ዓይነት የ“እምነት” ቅንጣት በውስጡ የለውም ማለት ግን ዘበት ነው፡፡ ምክንያቱም በሳይንስ ውስጥም የሚታወቁና የሚሰነዘሩ እውነታዎች በሙሉ ታይተው፣ ተሰምተው፣ ተቀምሰው፣ ተዳሰውና ተሸተው የታወቁ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያክል ከዘጠኝ ዓለማት (ፕላኔቶች) ውስጥ እስካሁን ያየነው አንድ እርሷም መሬት ነች፡፡ ሌሎቹ ጁፒተር፣ ማርስ፣ ሳቱርን ወዘተ. መኖራቸውን የምናውቀው አይተን ወይም ኑረንባቸው ሳይኾን ባለሞያዎቹ አለ ስላሉ ነው፡፡ “አልጌ” የሚባል እንስሳም ይኹን ተክል አይቼ አላውቅም፤ ባክቴርያ ተመልክቼ፣ ጠረኑም ሸትቶኝ አያውቅ፡፡ መኖሩን ግን አልክድም፤ ለምን ያጠኑ ሰዎች አሉ ስላሉ፡፡ ማንኛውም ሳይንሳዊ የእውነታ ድምዳሜ (Scientific Truth Claim) ከእምነት የጸዳ አይደለም፤ ማለት፣ አእላፋት ሳይንሳዊ ቅድመ ግምቶች ያለትምህርት እምልማዳዊ (ያለ sensory experience) “ይኾናል” ብሎ በማመን ብቻ ጥቅም ላይ እየዋሉ ሌሎች እልፍ ሳይንሳዊ የእውነታ ድምዳሜዎችን ለማምጣት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡
.
እዚህ ጋር በገቢር የምናየው በ“እምነት” መዋቅር ውስጥም ሳያዩና ሳይሰሙ መኖሩን መቀበል የሚባለው ነገር ስልተ ምክንያታዊ ውድቅነት (logical failure) ያለው ተደርጎ ሊታይ በፍጹም አይገባም ማለት ነው፡፡ ያለዚያ ሳይንቲስቶቹን በፍልስምናው ዓለም “የመለኪያ ምንታዌነት” (double standard መጠቀም) ወንጀል ውስጥ ይከታቸዋልና ያስፈራል፡፡
.
በዚያውም ላይ ደግሞ እነዚህ ሰዎች የእውነትን ምልዓት (በእምነትም በአመክንዮም የሚገኘውን) አያውቁም ማለት አይቻልም፡፡ ያውቃሉ፡፡ ከታወቀው በላይ ሌላ እውቀት፣ ከታመነው በላይ ሌላ እውነት እንዳለ ኹሉም ሰው፣ ሰው በመኾኑ ብቻ ያውቃል፡፡ በተለይ በተለይ ደግሞ “የእግዚአብሔር መኖር” በሰው ዘንድ ሊታወቅ ከሚችል ነገር ኹሉ ቀዳሚውና ወሳኙ እውነት ነው፡፡ ጠቢብ የሚያሰኘው እውነት ይህኛው ነው፡፡
.
ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ ለሮም ምእመናን በላከው መልእክት ላይ እሊህን እያወቁ በዐመፃ አላወቅንም የሚሉትን “እለ የአምርዋ ለጽድቅ ወይመይጥዋ በዓመፃሆሙ” ይላቸዋል፡፡ አውቀዋት እውነትን በዓመፃቸው የሚተኳት ማለት ነው፡፡ (ሮሜ.1፥18) ምክንያቱ ደግሞ ቀድመን እንዳልነው ነው፡፡ እነርሱ ያወቁትና የደረሱበት እውነት ራሱ የተገለጠበት ዓላማ ያልተደረሰበትና ያልታወቀው፣ ተስፋ የሚደረገው ታላቅ እውነት እንዳለ ማሳወቅ ነበር ግቡ፡፡ ከሚታየውና ከሚታወቀው ተነሥተው የማይታወቀውና የማይታየው እግዚአብሔር ከነዘላለማዊት መንግሥቱ መኖሩን አለማመን ኩነኔ ነው፡፡ በአጭሩ ከሰማይና ከምድር በውስጦቻቸው ካሉ ሥነ ፍጥረት በሙሉ የተሰወረውን የእግዚአብሔርን እውነት መረዳት በልቡናችን ላይ ተቀምጦልናል፤ ኹላችንም ነው፡፡
.
ሐዋርያው ከአመክንዮ ተነሥተን (ከሥነ ፍጥረት ተነሥተን) በእምነት ወደሚገኘው እውነት መሄድ እንዳለብን ሲያጸና --- “እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ዠምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ኾኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ኾኑ፥” -- ሮሜ.1፥18-21 ይላል፡፡
-------------------------------
ይቈየን!
መጋቢት 2008 ዓ.ም.