ብዙዎች ይህን ሥዕል “የማርያም ሥዕል” ይሉታል፡፡ የማያምኑ ወንድሞችና እኅቶች ደግሞ “የማርያም ሥዕል ታበዛላችሁ” ይሉናል፡፡ ሕፃን ሆኖ ሲያዩት ጊዜ ናቁት፤ በሥዕሉ ላይ እስከመኖሩም ረሱት፡፡ ሎቱ ክብር ወስብሐት ለእነርሱም ልቡና ይስጥልንና እመቤታችን የታቀፈችው ሕፃን ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው ሆኖ ጠፈሩን ሞልቶ ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡
በዘባነ ኪሩብ ሆኖ ጠፈሩን ያስተዳደረው እርሱ በእናታችን ማሕፀንም ሆኖ፣ በጀርባዋም ተኝቶ፣ በእቅፏም ተቀምጦ ፍጥረትን ሲያስተዳድርና የሰማዩን የምድሩን ሥርዓት ዐቃቤ ሆኖ ሲጠብቅ የነበረ ይኸው ሕፃን ነው፡፡ ይህ የማርያም ሥዕል አይደለም፡፡ የ“እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር” “እግዝእትነ ምስለ ፍቁር ወልዳ” እንጂ፡፡ እስኪ እንደዚህ እያልን እናመስግን
“ፈቃዱን ለሚሠሩ ልቡናቸውን ላቀኑ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው፡፡ ስሙን ለሚክዱ ለዓመፀኞች ሰዎች የሚበላ እሳት ነው፡፡ እሳታውያን የሚሆኑ ሱራፌልና ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻላቸው በእውነት እሳት ነው፡፡ ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን፤ ከፍ ከፍም እናደርግሻለን፡፡ እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና፡፡” (ቅዳሴ ማርያም ዘአባ ሕርያቆስ ዘሀገረ ብህንሳ)

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ