የደረስንበት ዘመን ክፉ ነው፤ ተጠራጥሮ፣ ተጠራጥሮ፣ ተጠራጥሮ ሲያበቃ … እናንተኑ መልሶ ይሸውዳችኋል፡፡
የሕዝቡን ክህደትና ለእግዚአብሔርም ኾነ የእግዚአብሔር ለኾኑ ነገሮች ያለውን ንቀት ስትመለከቱ የምር ግን “እውነት” አለች እንዴ ብላችሁ ራሳችሁን ትጠይቃላችሁ፡፡ እኔ በበኩሌ አንዳንዴ ጊዜው ቀን ሳለ ይጨልምብኛል፤ ቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እገባለሁ፡፡
“እውነትን” የሚናገራት አንድ ሰው ሳገኝ ደስ ይለኝና፤ አሃ እውነት አለች እላለሁ፡፡ የሕይወትን ውጣ ውረድ ዝም ብዬ እንደዚህ ከዘለቅሁት በኋላ፤ ወዲያው ጌታ ኢየሱስ ስለኋለኛው ዘመን የተናገረውን አስታውሳለሁ፡፡ ያንን ኹሉ የሚያስፈራ ዘመን፤ የሚያምነውም የሚክደውም የሚያብደው እብደት ኹሉ በወንጌል እንደተተነበየ አስታውሳለሁ፡፡ እውነት ለመናገር ያን ጊዜ ኹሉም ነገር ተመልሶ ቦታው ይሰካል፡፡ ዘመኑ ጥሩ ኾኖልኝ ሳይኾን፣ እንዲሁ የዘመናችን ቅጣምባሩ የወጣ ዓለም የግዴታ መከሰቱ የማይቀርና ሊቀ ካህናችን ኢየሱስም እንድንዘጋጅለት ያስጠነቀቀን ዓለም ነው፡፡
እርሱ ምን አለ መሰላችሁ፤ “ነገር ግን ጊዜው በደረሰ ጊዜ እኔ እንደነገርኳችሁ ታስታውሱት ዘንድ ይህን ነገርኳችሁ፤” ዮሐ. 16፣4፡፡ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እኮ አንድ ጊዜ እንኳ አርፋ አታውቅም፤ ኹል ጊዜ መሳደድ ላይ ነች፡፡ አባቶቻችን ታርደዋል፣ ተሰይፈዋል፣ ተከስክሰዋል፣ በሕይወት ሳሉ ቆዳቸው ተገፏል፣ እንደሽንኩርት ተቀርድደዋል፣ ለአናብስት ተሰጥተዋል ……… የኛ ዘመን መሥዋዕትነት/ሰማዕትነት የእነርሱን ሃይማኖት ጠብቆ፤ ቀድሞ በተማሩት ትምህርት ያመኑትን እምነት አጽንቶ መኖር ይመስለኛል፡፡ ትክክለኛ እምነታችን የሚፈተንበት ዘመን አሁን ነው፡፡
ወገኖቼ አንድ ነገር ልንገራችሁ፤ በዚህም ዓለም በሚመጣውም “ምንም … ከቶ ምንንንንን…ም አዲስ ነገር የለም፤ ኹሉም ነገር ያለና የነበረ፣ የታዘዘ … ነው፡፡ ደስ የሚለው ነገር ይህ ኹሉ እብደት ያልፋል፤ ኮሽኮሽታው ጸጥ ይላል፤ ወጀቡም አውሎውም ኹሉ በአንዲት የመለከት ድምፅ ድርቅ ብሎ ይቀራል … ሰላማችንን የነሳን ቅጣምባሩ ኹሉ ይጠፋል፤ ላይመለስ ያልፋል፡፡ ዛሬ በድንግዝግዝ እንደሚያይ ውዥብርብር ብሎብናል፤ ያን ጊዜ ግን …. በማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ ቃል … “ … ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን” 1ቆሮ. 13፣12
ክርስቲያኖች በፍጹም እንዳታዝኑ … የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይሁን! የእናቱን የእመቤታችንን ቃልኪዳን እያሰበ ዘወትር በረድኤት ይጠብቀን፤

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ