ሲኦል ሠርታ ትብላ



አንድ ኹለት … አንድ ኹለት …
ወደላይ ወደታች!
የዐይኖች ፍጥጫ … የግንባር ኩስትርትር … ፣
የጥርሶች ንክሻ … የእጆች መወጠር … ፣
ሆጵ! ሆጵ! …
ባካል ብቃት ሥራ ሥጋዬ ተዝናናች፡፡
ወዝ ገንዘብ አድርጋ ኪሎዋን ጨመረች፡፡
ከእስፖርቱም መብዛት ደም ግባት አገኘች፡፡
ታዲያ ምን ያደርጋል …
በጎ ጠባይዕ ሳይኖር ምግባር እየከፋ፣
ጅማትም ቢላቀቅ ቢለጠጥ ቢሰፋ፣
አጽዋማት ተገድፈው ጽድቅ እየተገፋ፣
ነፍስ ተቸግራ ለነግህ ያክል ተስፋ፣
በኪሎ ላይ ኪሎ ሲጨምር ሲፋፋ፣
ለዲያብሎስ ምሱን ለጅራፍ ቀሠፋ፣
ሲኦል ሠርታ ትብላ ኧረ የታባቷ!
ስለምን ይብዛላት ሥጋዬ እራቷ፤
እንግዲህስ ይቅር …
ከከብርጭቆ ውኃ አትርፌ ልጠጣ የጣመን አልብላ፤
ደም ለመለገስ ያህል ኪሎዬ ከሞላ፡፡
………………………………………………..…………………………………………..…………………………   

አስተያየቶች