እጅግ ደስ የሚያስሰኝ ታሪክ!
ለሰው ልጅ ከዚህ በላይ አስደሳች የምስራች ሊኖረው አይችልም --- አንብቡት
"እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው። ዘፍጥ. 3፣14 በአንተና #በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና #በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። ዘፍጥ. 3፣15 እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ። እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር አቆማለሁ፤ ዘፍጥ. 9፣8-9 የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥ እንዲህም አለው። እግዚአብሔር። በራሴ ማልሁ ይላል፤ ዘፍጥ. 22፣15 በእውነት
በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘፍጥ. 22፣15 ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና። ዘፍጥ. 22፣18
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር #ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። ኢሳ. 1፣9 #ሕፃን ተወልዶልናልና፥ #ወንድ_ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ #በዳዊት_ዙፋንና_በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ #ለሰላሙም_ፍፃሜ_የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። ኢሳ 9፣6-7 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ #ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ #ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም #አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ኢሳ. 7፣14 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ #ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል። ስለዚህ #ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ሚክ. 5፣1-3
እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር #ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን #ልጁን ላከ፤ ገላ. 4፣4 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት #ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ #አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች። መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ #ወንድ_ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም #ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን #የዳዊትን_ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ #ለዘለላም_ይነግሣል፥ #ለመንግሥቱም_መጨረሻ_የለውም። ሉቃ. 1፣26-31
ማርያምም እንዲህ አለች። ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል። ሉቃ. 1፣47-49
አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሐ. 5፣16-17 ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና። የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል። ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ ዮሐ. 5፣36-38 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ዮሐ. 5፣39 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ? ዮሐ. 5፣46-47
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው #ልጄ ይህ ነው፤ #እርሱን_ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ማቴ. 17፣5 በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም #እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ #እናት።የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም። አንቺ #ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ። #የሚላችሁን_ሁሉ_አድርጉ አለቻቸው። ዮሐ. 2፣1-5 ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ #እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ኢየሱስም #እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ #እናቱን። አንቺ #ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። #እናትህ እነኋት አለው። ዮሐ. 19፣25-27
ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት #ሴት ነበረች።ዘንዶውም #ሴቲቱ በወለደች ጊዜ #ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት #ሴት ፊትቆመ።ራእ. 12፣1 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ #ወንድ_ልጅ ወለደች፤ #ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ #ወንድ_ልጅ የወለደችውን #ሴት አሳደዳት። #ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች። በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ #እርሱም_የቀደመው_እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ #ወንድ_ልጅ የወለደችውን #ሴት አሳደዳት።ምድሪቱም #ሴቲቱን ረዳቻት፥ዘንዶውም #በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን #የኢየሱስም_ምስክር_ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ በባሕርም #አሸዋ ላይ ቆመ። ራእ. 12፣1-18
በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤ ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል። ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። #አሜን፥ #ጌታ_ኢየሱስ_ሆይ፥ #ና።" ራእ. 22፣18-20