ስንክሳር ዘወርኃ ሚያዝያ፡ “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ”


ሚያዝያ ፲፩

የሚከተለው ጽሑፍ በሚያዝያ ዐሥራ አንድ ቀን 2007 ዓ.ም. በሊብያ ሰማዕታት ለኾኑት ለኢትዮጵያ ሰማዕታት መታሰቢያ ይኾን ዘንድ የቅዱሳንን መታሰቢያ በሚያትተው መጽሐፈ ስንክሳር ዘይቤ በማይታወቅ ጸሐፊ ተጽፎ የተገኘና በማኅበረሰብ ድረ ገጾች የተገኘ ጽሑፍ ነው፡፡ በመሠረቱ ይህን ማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ሲኾን ነገር ግን ለምክረ አሳብ ይረዳ ዘንድ በዚህ መልክ በዚህ ድረ ገጽ ቀርቧል፤ ለአስተያየት ክፍት ነው፡፡ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን፡፡
ዘለምጽ ወታኦድራ መኰንን፡፡ እግዚአብሔር ይምሐረነ በጸለቶሙ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡
የመኮንኑ የታኦድራ፡መታሰቢያቸው ነው፡፡ እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ለዘላለሙ ይማረን አሜን፡፡
፲፬፤ወበዛቲ ዕለት አዕረፉ ዕሥራ ወስምንቱ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ።
፲፭ከመዝ ኮነ በውስተ  ሀገረ ሊብያ በዕሥራ ምዕት ወሰብዐቱ ዐመተ ምሕረት። በአሜሃ ዘመን ተንሥኡ ተንባላት እለ ስሞሙ አይሲስ በውስተ ሀገረ ኢራቅ ወሶርያ  ሊብያ ወየመን። አሐዙ ይቅትሉ ሰብአ ዘረከቡ ወፈድፋደሰ እለ ኮኑ ክርስቲያነ በእምነቶሙ። ብዙሓን ክርስቲያን ተመትሩ አርእስቲሆሙ በአይሲስ ወተወክፉ አክሊለ ስምዕ እምእላ ሀገራት።
፲፮፤በዝ ዘመን ውእቱ ዘረከቦሙ አይሲስ ለሰብአ ኢትዮጵያ በውስተ ሀገረ ሊብያ እንዘ የሐውሩ ኀበ ሀገረ ኢጣልያ በእንተ መፍቅደ ልቦሙ። እሉሀድያን ውሉደ ሰይጣን ወአራዊተ ገዳም አሐዝዎሙ ወአዘዝዎሙ ወአፍርሕዎሙ ከመ ይክሀዱ ስሞ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት።
፲፯፤ወእምዝ ዘበጥዎሙ በዘዚአሁ ዝብጠታተ በእንተ ዘኮኑ ክርስቲያነ ርእዮሙ ማዕተበ ክሣዶሙ። ውእቶሙሰ አበዩ ይእዜኒ ክሂደ ሃይማኖቶሙ እመኒ አመከርዎሙ በረሐብ ወጽምዕ ወበካልኣን ኵነኔያት። ሶበ አበዩ ክሂደ ወሰድዎሙ ኀበ ምድረ በድው ኀበ አልቦ እክል ወማይ ከመ ይእመኑ እምጽንዐ ረሐብ ወጽምዕ። ወእምዝ ጠየቅዎሙ ከመ ይብትኩ ማዕተበ ክሣዶሙ ወይክሀዱ ስሞ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ።
፲፰፤እሉሰ ሰማዕታት ይእዜኒ አበዩ ክሂደ ስሞ ለፈጣሪሆሙ። አዲ ይቤልዎ ለአይሲስ " አይሲስ ለእመ ክህልከ ቀቲሎታ ለሥጋነ ኢትክል ቀቲሎታ ለነፍስነ። ኢንፈርሕሂ ወኢንደነግጽ እምብልሐ ሰይፍከ እስመ አቅዲሙ ነገረነ አምላክነ እንዘ ይብል ኢትፍርሕዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ።
፲፱፤አዲ ይቤለነ በውስተ ወንጌሉ ቅዱስ እስመ ኵሉ ዘከቀተለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመሥዋዕተ ያበውእ። ይእዜኒ አንተ ላእኩ ለዲያብሎስ ፈጽም ላዕሌነ መልእክተከ ሰይጣናዌ ወአብእ መሥዋዕተከ ርኩሰ ለእምላክከ ሰይጣናዊ። ንህነኒ ናበውእ ክሣደነ ንጹሐ ለእምላክነ ዘፈጠረነ እስመአምር ዘከመ ያነሥአነ በትንሣኤሁ ቅድስት አመ ዳግም ምጽአቱ።”
፳፤አይሲስኒ አላዊ መተሮሙ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወኮኑ ሰማዕተ በከመ ዛቲ ዕለት። ወእምዝ ተሀውከት ኵላ ኢትዮጵያ ወኵላ ዐለም እስመ ተርእየእይንተ ጥብሐቶሙ ለሰማዕታት በመስኮተ ትእይንት። ኵሎሙ ሰብአ ኢትዮጵያ አስቆቀዉ ወበከዩ ብካየ መሪረ እንዘ ይገብሩ ሰላማዌ ትእይንተ በበአዕዋዲሁ ወበበፍኖቱ። ወይብሉ በበቃሎሙ "አይሲስ አይሲስ እንተ ትቀትሎሙ ለሰማዕታት: ወታውሕዝ ደመ ንጹሓን በበፍናዊሁ ከመ ደመ አክልብት: ይደልወከ ትቁም ውስተ ዐውደ ፍትሕ ሰማያዊ።"
፳፩፤በዝንቱ ዘመን ቈስለ ልቡ ለሕዝብ በኀዘነ ሥጋ እስከነ ይብል "ፍትሐ ጽድቅ ዘዐርገት ውስተ ሰማይ ከመ ትንበር ምስለ ዘፈጠራ እግዚአብሔር እስመ ኢረከበት ውስተ ዛቲ ምድር ኀበ ትነብር ወኀበሂ ታጸልል። ናሁ ይጸርሕ ደሞሙ ለሰማዕታት ቅድመ ገጹ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት ከመ ይረድ ፍትሐ ርትዕ ዲበ ምድር ወይሠረው አይሲስ እምውስተ ገጻ ለምድር።"
፳፪፤በረከቶሙ: ወጽንዐ ገድሎሙ ለእሉ ሰማዕታት ይኅድር ላዕሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን።

፲፬፤በዚህችም ዕለት ሃያ ስምንቱ የኢትዮጵያ ሰማዕታት ዐረፉ፡፡
፲፭፤በሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምሕረት በሊብያ ሀገር ውስጥ እንዲህ ሆነ፡፡ በዚያም ዘመን ስማቸው አይሲስ የተባለ ጨካኞች በኢራቅና ሶርያ በየመንና ሊብያ ሀገራት ተነሡ፡፡ ያገኟቸውንም ሰዎች ይልቁንም ደግሞ ሃይማኖታቸው ክርስቲያን የሆኑትን ይገድሏቸው ዘንድ ይይዟቸው ነበር፡፡ በእነዚህ ሀገሮች ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በአይሲስ እየተመተሩ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ፡፡
፲፮፤በዚያም ዘመን በሊብያ ሀገር አይሲስ ያገኛቸው የኢትዮጵያ ሰዎች የልባቸውን መሻት ሊፈጽሙ ወደ ሀገረ ኢጣልያ ሲጓዙ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚያም ከሀዲዎች የሰይጣን ልጆችና የበረሃም አውሬዎች ያዟቸውና የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እንዲክዱ አዘዟቸው፤ አስፈሯቸውም፡፡
፲፯፤ከዚህም በኋላ በአንገታቸው ላይ ማኅተም እንዳሰሩ ያዩአቸውን ክርስቲያን የሆኑትን ደበደቧቸው፡፡ እነርሱ ግን ሃይማኖታቸውን መካድ እምቢ ባሉ ጊዜ ዳግመኛ በረሐብ፣ በጥምና በሌላም መከራ ፈተኗቸው፡፡ መካድን እምቢ ባሉ ጊዜ ከረሐብና ጥም ጽናት የተነሣ እንዲያምኑ መብልና መጠጥ በሌለበት ምድረ በዳ ወሰዷቸው፡፡ በዚያም የአንገታቸውን ማኅተም በጥሰው የእግዚአብሔርን ስም እንዲክዱ ጠየቋቸው፡፡
፲፰፤እነዚያ ሰማዕታት ግን አሁንም የፈጣሪያቸውን ስም መካድን እምቢ አሉ፡፡ ይልቁንም እንዲህ አሉ “አይሲስ ሆይ ሥጋችንን መግደል ቢቻልህም ነፍሳችንን መግደል አትችልም፡፡ አስቀድሞ አምላካችን ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሩ ነፍሳችሁን ሊገድሏት አይቻላቸውምና ብሎ ነግሮናልና የሰይፍህንም ግርማ አንፈራም፡፡
፲፱፤ደግሞም በቅዱስ ወንጌሉ የሚገድላችሁ ሁሉ መሥዋዕትን እንደሚያገባ ይመስላል አለን፡፡ አንተም የዲያብሎስ መላክተኛ የረከሰ መሥዋዕትህን ለሰይጣናዊ አምላክህ አግባና ሰይጣናዊ መልእክትህን ፈጽም፡፡ እኛስ በዳግም ምጽአቱ በቅድስት ትንሣኤው እንደሚያነሣን ስለምናውቅ ንጹሕ አንገታችንን ለፈጠረን አምላክ እናገባለን፡፡”
፳፤በዚህችም ዕለት አረመኔው አይሲስ ራሶቻቸውን በሰይፍ መተራቸውና ሰማዕታት ሆኑ፡፡ ከዚህም በኋላ የመጽናታቸው ትእይንት በመስኮተ ትእይንት ታይቷልና መላዋ ኢትዮጵያና ዓለም በሙሉ ታወከ፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች ሁላቸው ሰቆቃ አገኛቸው በየአደባባዩና በየመንገዱም ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ መሪር ልቅሶ አለቀሱ። ሁሉም በቃላቸው አሰምተው “አይሲስ አይሲስ አንተ ሰማዕታቱን የገደልሃቸውና የንጹሐንንም ደም እንደ ውሾች ደም በየመንገዱ ላይ ያፈሰስክ በሰማያዊ የፍርድ አደባባይ ትቆም ዘንድ ይገባሃል፡፡” አሉ፡፡
፳፩፤በዚያም ዘመን “በምድር የምታርፍበት ስላላገኘች ከፈጠራት ከእግዚአብሔር ጋር እንድትሆን ወደ ሰማይ የወጣች የእውነት ፍርድ አሁንም ታረብባለች፡፡ አሁንም ቀጥተኛ የሆነች ፍርዱ እንድትወርድና ይህም አይሲስ የተባለ ከምድር ገጽ ይጠፋ ዘንድ የሰማዕታቱ ደም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ይጣራል” እስከሚሉ ድረስ የሕዝቡ ሁሉ ልብ በሥጋ ኀዘን ቈሰለ፡፡
፳፪፤የእነዚህ ሰማዕታት በረከታቸውና የተጋድሏቸው ጽናት በእኛም ላይ ለዘላለሙ ይደርብን አሜን።

አርኬ፡
ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ። ምስለ ሰማዕታት ዘግብጽ መከራቲክሙ ዘሐብራ። ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶሳዊት ሐራ። እፎ ክህልክሙ ተዐግሦ ጽኑዕ መከራ። እስከ ክሳውዲክሙ በአይሲስ ተመትራ።