ዘከመ ዐርገ እግዚእነ |
ርሱማ
ቀድሞም ዐርጎ ነበር …
አሁን
ግን …
ምድርን
የፈጠራት ርሱ ስለኾነ ይዛ አላስቀረችውም፡፡ በክብር ከፍ ከፍ ብሎ ሄደ፡፡ ሰማይን ያበጀው ርሱ ስለኾነ ሰማይ አልራቀውም፡፡ በክብር
ወደ መጣበት ዐረገ፡፡
ከዚህ
ቦታ አለ፣ ከዚህ ቦታ የለም የማይባልለት መለኮት ስለኾነ ከላይ ወደ ምድር መጣ ማለት እንደማይገልጸው ኹሉ ከምድርም ወደላይ ወጣ
እንዲሁ አይባልም፡፡
ነገር
ግን ስለፍጹም ተዋሕዶ ምክንያት … ያለው ክርስቶስ አንድ ስለመኾኑ ምክንያት …
በብርሃናት
መላእክት ፊት ተቀምጦ መመለክን በአደባባይ ርቃኑን ሊሰቀል ወደ መዋረድ ትሕትና፣
መላእክት
ፊቱን ማየት የማይቻላቸው እሳት መለኮቱን ጭፍሮች ፊቱን እስኪጸፉት ወደተዋረደበት ትሕትና፣
መናፍስት
ከመለኮቱ እሳትነት ተፈጅተው እንዳይጠፉ በክንፎቻቸው ራሳቸውን የሚጋርዱለት ጌታ ጭፍሮች ልብሱን ሊገፍፉት እስኪችሉ የደረሰበት ትሕትና፣
በዘባነ
ኪሩብ በዙፋን መቀመጡን እንደወንበዴ በመስቀል ላይ ሊቸነከር በፈቀደበት ትሕትና መደበቁ ቀርቶ .. ይኸውም በመዝገብ ቀርቶ አሁን
ግን በልዕልና፣ ለዐይን በሚታይ የጎላና የተረዳ ከፍ ማለት ከፍ ብሎ ወደ ክብሩ ስፍራ ተመለሰ እንደ ማለት ነው፡፡
ነገሩማ
ርሱ ቀድሞም ዐርጎ ነበር፡፡
ቃል
ከዙፋኑ ወርዶ በድንግል ማሕፀን ሲፀነስ በዚያው ቅጽበት ሥጋ ከድንግል ማሕፀን ደግሞ ወጥቶ በአብ እሪና በዙፋን ያኔውኑ ተገኝቷል፡፡
ቦታ የማይወስነው መለኮት ከላይ ሳይጎድል ወደ ምድር በወረደ ጊዜ፣ ሥጋም የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ከምድር ሳይጐድል
በሰማይም ምሉዕ ኾኗል፡፡
እዚህ
አለ እዚያ የለም የማይባለው ስፉሕ እና ምሉዕ በኵለሄ በኹሉ የመላ መለኮት በምድር ሳይጨመር ከባሕርያችን ሲወለድ ውሱኑ ሥጋ ደግሞ
የመለኮትን ገንዘብ ከንዘቡ በማድረጉ በሰማይም ሳይጨመር በተዋሕዶ ተገኝቷል፡፡ በሰማይም በምድርም ያለው ክርስቶስ ለየቅል ያይደለ
አንድ ብቻ ስለኾነ፣ ርሱ ደግሞ ሥጋን ፈጽሞ የተዋሐደ አንድ ባሕርይ፣ በቦታና በጊዜ ውሱን ያልኾነ ነው፡፡
“አልቦ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ላይ የወጣ የለም” እንዳለ ዮሐ.3፣13 ከሰማይ ወደ ምድር
በወረደበት ቅጽበት ከምድርም ወደ ሰማይ ያኔዉኑ ወጥቷል፡፡
ዛሬሳ!
…
ዛሬማ
እንዲያ በረቀቀ በተዋሕዶ ምሥጢር ብቻ ሳይኾን ለዐይን በሚታይ ከፍታ፣ በግዘፍ፣ በጎላና በተረዳ ከምድር ከፍ ከፍ ብሎ ወደ ቅድም
ክብሩ መመለሱን ሊያሳይ ዐርጓል፡፡
እንዲሁ
ደግሞ ሊፈርድ ይመጣል …
“ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ አምላክ በእልልታ
ወደ ሰማይ ወጣ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፤ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤” መዝ.46፣5-6፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ